ባለፈው ዓመት ዕጣ የወጣባቸው የ20/80 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለዕድለኞች ሊተላለፉ ነው

የሪፖርተርን ዘገባ ከዚህ በታች ያንብቡት

ከዓመት በፊት የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ የወጣባቸው ከ32,000 በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ዕጣ ለወጣላቸው ዕድለኞች ሊተላለፉ ነው፡፡

ዕጣው በወጣበት ወቅት ቤቶቹ የተገነቡት በኦሮሚያ ክልል እንደሆነ በመግለጽ ውዝግብ በመነሳቱና ቤቶቹን ማስተላለፍ ባለመቻሉ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ የተነሳውን የውዥንብርና ውዝግብ በማጥናት፣ የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጭምር ትዕዛዝ መሰጠቱ የሚታወስ ቢሆንም፣ ላለፉት አንድ ዓመት ግን ለሕዝብ ምንም የተገለጸ ነገር አልነበረም፡፡

ኮሚቴው ባደረገው ጥናት ዕጣ ከወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ 9,000 ቤቶች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ መገንባታቸውን አረጋግጦ፣ ለአስተዳደሩና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማቅረቡን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡  በመሆኑም በከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ ተረፈ ፊርማ ሰሞኑን ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተያዘው ወር ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች ይተላለፋሉ፡፡ ነገር ግን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰን ላይ የተገነቡ ቤቶች ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ተነጋግሮና መፍትሔ አስቀምጦ ስምምነት ላይ ሳይደረስ፣ ቤቶቹን ለዕድለኞቹ ለማስተላለፍ ውል መፈጸም በቀጣዩ ሒደት ላይ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ቤቶቹ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ አማካይነት ውል ተፈጽሞባቸው ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ፣ ወደፊት የሚያስተዳድራቸው የኦሮሚያ ክልል በመሆኑ እንዴት እንደሚሆን በተለይ ጥናቱን አጥንቶ ያቀረበው ኮሚቴ ሊያብራራ ይገባ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

Read more 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s