በቴሌቪዥን  ለሃይማኖት ተቋማት የተሰጠውን የአየር ጊዜ በተመለከተ ከአለም አቀፍ የዋቄፈና ጉባኤ የተሰጠ መግጫ

ለኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር

ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

አዲስ አበባ

መጋቢት 28 ቀን 2012

ጉዳዩ፣ በቴሌቪዥን  ለሃይማኖት ተቋማት የተሰጠውን የአየር ጊዜ ይመለከታል

በቀን 27.08.2012 ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በተጻፈ ደብዳቤ በሀገሪቷ ውስጥ ያሉት የሃይማኖት ተቋማት  በሙሉ ለህዝቡ የኮሮናን በሽታ በተመለከተ ትምህርት አንዲሰጡ የአየር ጊዜ በዝርዝር ይደለድላል።

ይህ አኩሪና ጥሩ እርምጃ ነው። ሁሉም የእምነት ተቋማት አገሪቷ አደጋ በተጋረጠባት ጊዜ የተለየ ግዳጅ አለባቸው። ይህም ግዳጅ ህዝቡን ማስተማር፣ ማበረታታት፣ ማረጋጋግትና መንገድ መምራት ናቸው። ይህንንም ግዳጃቸውን እንዲወጡ በማስ ሚዲያ የአየር ጊዜ መስጠቱም ትክክለኛ ስለሆነ የምናደንቀው ይሆናል።

ይህን እንጂ በዚሁ ደብዳቤ ላይ የተመለከትነው ጉዳይ እጅግ አሳዝኖናል። ይሀውም በዚህ ክፉ ጊዜ የዋቄፈና እምነት ተቋም ይህንን ግዳጅ እዳይወጣ እድል መነፈጉ ነው። በዚሁ ደብዳቤ ላይ እንደምያሳየው በሀገሪቷ ውስጥ የሚገኙ የእምነት ተቋማት በሙሉ በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ አራት የቲቪ ጣቢያዎች (ኢቢሲ፣ አዲስ ቲቪ፣ ዋልታና ፈና) የተደለደለላቸው የጊዜ ሰሌዳ ነው። ይሁን እንጂ ዋቄፈና ይህ እድል አልተሰጠውም። ይህም የሚያመለክተው የዋቄፈና እምነት ተከታዮችን መብት መጋፋትና ለዘመናት ሲደረግ የነበረው ጭቆና ሲደገም ያሳያል።

አለም አቀፍ የዋቄፈና ጉባኤ እንደሚረዳው ለዘመናት የነበረው ጭቆና በህዝብ ትግል የተገረሰሰ ቢሆንም አሁንም ግን ጭቆናው ሙሉ በሙሉ ያልተጠረገ መሆኑን ነው። ይህ ግን በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት ተቀባይነት የለውም። በህገ መንግስቱ መሰረት ሁሉም እምነቶች እኩል ናቸው።

በተለያዩ ጊዜያት የዋቄፈና እምነት ተከታዮች የስነ ቀብር ቦታ በማጣት ይህንንም ከሌሎች የእምነት ተቋማት ገዝተው ሲጠቀሙ መቆየታቸውንና ይህንንም ለጠቅላይ ሚኒቴር ቢሮ አቤቶታ አቅርበን መልስ የተነፈግን መሆኑን መግለጽ እንወዳለን።

አለም አቀፍ የዋቄፈና ጉባኤ በሰው የተፈጠሩ ችግሮች በሰው ይፈታሉ ብሎ ያምናል። ችግሮችንም ለመፍታት በመልካም መንፈስ ነገሮችን ማየትን ይጠይቃል። ስለዚህ ዋቄፈናም አንደሌሎቹ የእምነት ተቋማት ክብርና የሚገባውን ቦታ እንዲሰጠው በአብሮት እንጠይቃለን። የኮሮና በሽታን ለመዋጋትም የሚገባውን የአየር ጊዜ ያለ አድልዎ እንዲሰጠው አጥብቀን እንጠይቃለን። የሚመለከተው የመንግስት ተቋምም ይህንን በአጭር ጊዜ አንድያስተካክለው በመላው የዋቄፈና እምነት ተከታዮች ስም በአክብሮት እንጠይቃለን።

ክብርና መረባ በሁሉም ፍጥረታት ላይ ይደር

አስናቀ ተ ኢርኮ

ዋና ፀሃፊ                                                                                                                      ግልባጭ

አለም አቀፍ የዋቄፈና ጉባኤ                                                          International Oromo Inter-faith Network

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s