ኢትዮጵያ ያወጀችው ጦርነት ፡ ወዴት ያመራል?

ኢትዮጵያ በብዙ ግምባሮች ጦርነት በህዝቦቿ ላይ ኣውጃለች። ከሁለት ኣመታት በፊት በኦነግ ጦር ላይ፣ ከ4  ወራት በፊት በኦሮሞ ህዝብ ላይ በግልጽ ጦርነት መታወጁ ይታወሳል። ትናንት በ03.11.2020 በትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት ታውጇል። ጦርነቱን ያወጀው የነፍጠኛው ስርኣትና ደጋፊዎቹ ናቸው።

ይህ ጦርነት የኢትዮጵያና ህዝቦቿ ሳይሆን በኣማራ ክልል መንግስት የሚደገፍ በመንግስት ስም የሚንቀሳቀስ ቡድን ጦርነት ነው።

ከሁለት አመታት በፊት የኦነግን ሰራዊት በሁለት ወራት ውስጥ እናጠፋለን ብሎ የሚፎክረው ጀ. ብርሃኑ ጁላ ማጥፋቱ ቀርቶ ዓይኑ እያየ ፊንፍኔን እየተቃረቡ ነው። በትጥቅና በጀት ያልተደራጀው ሰራዊት መንግስት ነኝ ባይን እያሸነፈ ይገኛል። የሃጫሉን ግድያ ተከትሎ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የተከፈተውም ጦርነት ውጤቱ ኣገር ማፍረስ መሆኑ ግልጽ ሆኗል። ትናንት በትግራይ ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍተዋል። ይህን ጦርነት ያወጀው በነፍጠኛ ቡድን የሚመራው መንግስትና የኤርትራ መንግስት ነው። ለዚህም ጥርነቱን የተከፈተው በትግራይና በኣማራ ክልል ድንበር ነው።

ምን ሊከሰት የችላል?

  1. የኢትዮጵያ መንግስት ትልቅ ምስቅልቅል ውስጥ ይገኛል፣ ተገዶ ከሚማገድ በስተቀር ወዶ የሚዘምት የለም። ያለው ድጋፍ ከኤርትራ መንግስትና ኣማራ ክልል ብቻ ነው።
  2. የትግራይ ህዝብ ጦርነትን ያውቅበታል። ለሃያ ዓመታት ታግሎ ነው ደርግን ያሸነፈው። ያውም እንደ ዛሬ ኢኮኖሚ ሳይኖረው ነበር። መሬቱም ለመከላከል ያመቸ ነው። መሬቱን ከማንም በላይ ያውቁታል። ሰማንያ በመቶ የሚሆነው የሀገሪቷ ጦር መሰሪያ በትግራይ ክልላዊ መንግስት እጅ ይገኛል።
  3. ማንኛውም ጦርነት በቀላሉ በኣጭር ጊዜ ኣይቆምም። ረጅም ጊዜ ይወስዳል። ኢትዮጵያም ትሁን ኤርትራ ለረጅም ጊዜ የሚያዋጋ ኢኮኖሚ የላቸውም። የውጪ እርዳታ ይቆማል፣ የኣገርቱ ምርት በጦርነቱ ምክንያት ይቀንሳል። ጦርነት ደግሞ ከፍተኛ ኢኮኖሚ ይጠይቃል። በየሴኮንዱና በየደቂቃል በሺዎች የሚቆርጠር የሰው ነብስና በሚሊዮን የሚቆጠር ሃብት ይወድማል።
  4. አንደኛና ሁለተኛውን ነጥንብ ስናነጻጽር ይህ ጦርነት ዓብይ ኣህመድ ከስልጣን ተባሮ ኣገርቷ ቀውስ ውስጥ ጋብታ፣ ኤርትራም ተዋርዳ፣ ወያኔ እንደ ኣዲስ ኣዲስ ኣበባ መጥታ ያከትማል።

ይህ ጦርነት ኦሮሞናን ብሄር ብሄረሰቦችን ለትግራይ ህዝብ ካላቸው ሃዘኔታ በስተቀር ኣይመለከታቸውም። መዋጋትም ኣያስፈልጋቸውም። ማድረግ ያለባቸው ኣካባቢያቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ማጽዳትና ኣገርን መቆጣጠር ነው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s